መጋቢት 1ቀን 2005 ዓ.ም.
የአባይ ግድብ ፣ሚለኒየም ግድብ፣ህዳሴ ግድብ፣ባለራዕዩ መሪያችን ግድብ፣መለስ ዜናዊ ግድብ፣ዓባይን የደፈረ መሪ ግድብ፣ወዘተ እየተባለ የስለት ልጅ ይመስል የተለያየ ስያሜ የተስጠው ግድብ ዋናው ዓላማ ከወያኔ የጫካ ማኒፌስቶ ጋር የተያያዘ መሆኑ መርሳት የለብንም፣ በየግዜው እንደተገለፀው ኢትዮጵያን በዘር፣በሃይማኖት፣በብሄረስብና ቓንቓ በመከፋፍል አንድነትና ህብረት እንዳይኖረው እንዳይረዳዳ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት ብዙ ጥሯል ይህ የተጠበቀውን ያህል ውጤት አላመጣ በማለቱ አገሪቷን ጦርነት ውስጥ ለመክተት የታቀደ ነው፣ከአዋሳኝ አገሮች ይልቅ ታሪካዊና ጠንካራ ጠላታችን ግብፅን የሚያስቆጣና ቅፅበታዊ እርምጃ እንድትውስድ የሚያደርጋትን ዓባይ እገድባለሁ ብሎ መፎከርና መሯሯጥ ነው፣ በዚያ ላይ የመለስ ዜናዊ ፀሃይ በማሽቆልቆል ላይ ነች፣ ብዙ ግዜ ስልጣን የሚወዱ አምባገነኖች መውደቂያቸው ሲደርስ ችግር እንዲፈጠር ይሻሉ፣በመሆኑም ለክፉ ቀን ያስቀመጣትን የመጨረሻ ካርዱን በዓባይ ላይ መዘዛት፣ መለስ ዜናዊ ዓባይን ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስትያንና ገዳማትን እንዲሁም መስጊዶችን የደፈረ ቀንዳም ስይጣን ነው እያለ የአዲስ አበባ ህዝብ ስላማዊ ስልፍ ቢከለከል በየዓመቱ በታላቁ ሩጫ ስሜቱን በጩኸት እንደገለፀ ነው፣ አገሪቱን ከጦርነትና ከችጋር አዙሪት እንዳትወጣ ማድረግም የዘወትር ህልሙ ነው፣ ቀኑ የማይደርስ መስሎት በዓለም ሚዲያዎች ሁሉ የመጨረሽ ጊዜየ ነው ከዚህ በሁዋላ ምርጫ ውስጥ አልገባም እያለ ማሳወቁ ፍፃሜው መድረሱ አስጨንቆታል፣ አስደንግጦታል፣ ስለዚህ ይህ ቅንነት የጎደለው ስው የኢትዮጵያን ህዝብ የበለጠ ጥፋትና እርስ በርሱ አመስቃቅሎ መሄድ ሞት ቀደመው እንጂ የመጨረሻው አጀንዳው ነበር፣ ሁለተኛው በዚህ ግድብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ መስብስብና አዲስ ከተማ በሩቅ ምዕራብ መመስረት ነው።ይህም በከተሞች ያለውን የህዝብ ብዛት ለመቀነስ ይረዳል፣ ለዚህም በውዴታም በግዴታም ከህዝቡ ከፍተኛ ገንዘብ መስብስብ፣ ይህም ህዝብን አራቁቶ የወያኔ ቅን አገልጋይ ማድረግ፣ ለዚህም ሚዲያዎች ዋናውን የቅስቀሳ ስራ ያለመታከት እንዲስሩ ማድረግ፣ሌት ተቀን ፕሮግራሙ ዓባይ ብቻ እንዲሆን፣ ህዝቡን ማሳመን፣ በግድ እንዲቀበል ማድረግ፣ማስልቸት፣በቲያትርና ዘፈን ማዘናጋት፣
የዓባይ ግድብ ህዝብ መዝረፊያና ማፈናቀያ ነው
የኢትዮጵያ ህዝብ የድህነት ደረጃ መስፈርቱን በማለፉ ደረጃ አልባ ሆኗል ማለት ይቻላል፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሌሊት ለሚነሳ ስው በየፌርማታው ፌዴራል ፖሊስ አስከሬን ሲስበስብ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም፣ በዓባይ ህዝቡን ማደህየት ከጀመረ ይኸው ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል፣ ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ይራወጥ እንዲሉ ምኑም ሳይያዝ ገና ከጅምሩ ዓለም ይወቅልን ዓባይን ገደብነው አዋጅ ቀረሽ ዕወቁልን ማስታወቂያ ጧት ማታ በሬድዮና ቴሌቪዥን መለፈፍ አንድም ህዝቡን ማስፈራራት ሁለትም ጦር አምጣ ነው ማለት ይቻላል፣ አሁንም አልተቁዋረጠም፣ ጥንት አባቶቻችን ሙያ በልብ ነው ይሉ ነበር በርግጠኝነት የሚያደርጉትን ነገር ሲገልፁ፣
በመጀመርያ-- ግድቡ ፍፃሜ እንደሌለው ከጅምሩ ያስታውቃል፣ ዓላማው ግን በመዋጮ ስም ህዝቡን ማደህየት ነው፣ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ንብረት እንዲያፈራ በፍፁም አይፈልግም፣የቁዋጠራትን ጥሪቱን ከጉያው መንጭቆ መውስድ ነው፣ ባለፉት ዓመታት በተለያየ ቅስቀሳ በቤት ስራ ማህበር፣በኮንዶሚኒየም ቤት፣በባንክና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሼር ግዢና በተለያዩ ኩባንያዎች ሼር ግዙ አየተባለ ገንዘብ አደባባይ እንዲወጣ ተድርጉዋል፣ ይህም ወያኔ ሃብት ያለበትን አድራሻ ለማወቅ ጠቅሞታል፣ የአገሪቷን ሃብት መቆጥጠርም አስችሎታል፣ የነጋዴውን ሃብት ቀደም ሲል ደርሶበታል፣ አሁን ህዝቡን በግድቡ ስም መዋጮ መጠየቅና የመጨረሻ ድህነት አዘቅት ውስጥ መክተትና ዘላለማዊ ለማኝ አድርጎ መግዛት ነው፣ ይህም ተሳክቷል።
ሁለተኛ--ወያኔ አገሪቷን በዘጠኝ ክልል መከፋፈል ብቻ ሳይሆን ነፍጠኛና መጤዎችን ከክልልህ አስወግድ በተባለው መመርያ መስረት በርካታ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ከኖሩበት ልጆች ወልደው ከብደው፣ሃብት ንብረት አፍርተው በፍቅርና ወዳጅነት በስላም ከሚኖሩበት ቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጉዋል፣ይህም ህዝቡ ወደ ከተሞች በተለያየ ምክንያት ተገዶ ፈልሷል፣ ይህም ህዝብ ወደ ከተሞች እንዲፈልስ አድርጉዋል ዕድገቱም በሃያ ዓመታት ውስጥ አስደንጋጭ አድርጎታል፣ መፍትሄውም በዓባይ ግድብ ስም አዲስ ከተማ መፍጠር፣ ስለዚህ ከአዲስ አበባና ክልል ከተሞች ስራ አጡን፣ቤቱ እየፈረስ መጠለያ ያጣውና በገጠር ደግሞ የርሻ መሬቱን እየተነጠቀ ወደ ከተማ የሚጎርፈውን ወደ ዓባይ ከተማ እንድሄድና ከከተማ አካባቢ እንዲርቅ ማድረግ ነው።
የሳውዲ ሚኒስትር መልዕክት ምንድነው?
እውን ግብፅ ዓባይ እየተገደበ ዝም አለች? እያንዳንዷን ክንዋኔ እንደሚከታተሉ ይታወቃል፣ መጀመርያ ስሞን የግብፅ መልዕክተኞች በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ ተመላልስዋል፣ በመስረቱ ግብፆች አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲያቸው ከአንድ ሻምበል ያላነስ የስለላ ኃይል እንዳለ ይታመናል፣በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት ኤኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ(UNECA)፣ በአፍሪካ ህብረትና አዲሰ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚስሩ፣ በህክምናና በተለያየ ስራ የሚኖሩ ግብፃውያን ቁጥር ቀላል አይደለም፣ ይህ ሁሉ ስው በዓባይ ዙርያ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ በተጨማሪ በርካታ ግብፃውያን ግድቡ የሚስራበትን ቦታ ሄደው ኣንዲጎበኙ ተደርጉዋል፣ በማንኛውም ግዜ እንዲጎበኙም ተፈቅዶላቸዋል፣
ሱዳኖቹ ግን ከፕሬዚደንቱ ጄ/አልበሽር ጀምሮ አዲስ አበባ መኖሪያቸው ኢትዮጵያም ሁለተኛ ቤታቸው ነች፣ ግድቡም የተስማሙበት ይመስላል፣ ግብፅን እርምጃ እንደምትወስድ ስለሚያቁ፣ እዚያው አጠገብ የአየር ኃይል መደብ(AIR BASE) ግብፆች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ዓላማው አንድ በመሆኑ፣ ከጎንደርና ጎጃም የርሻ መሬት ቆርሶ ለሱዳን ተስጥቷል ቦታውም በ50ኪ.ሜ. ስሜን ሲገኝ፣ ከዋናው የሱዳን ጠረፍ ደግሞ በ 10ኪ.ሜ. ለሳውዲ ስታር ብዚነስ ግሩፕ የተስጠው ደግሞ 30ኪ.ሜ. ደቡብ ይገኛል፣ ይህ የሚያመለክተው የግድቡን ስራ የአረቦች በቅርብ ርቀት ይከታተላሉ፣ ታድያ ውሃ ሳይሆን ሌክ ናስርን ያስቸገረው ደለል ማጠራቀሚያ ካልሆነ በቀር ግብፅ በፀጥታ አትመለከተውም፣ በዚህ ዙርያ ሙያተኞች ሃሳብ ሊስጡበት ይችላሉ፣ መለስ ዜናዊ ራሱ ያስባል ራሱ ይፈፅማል የሚያማክረው፣ ሃሳብ የሚያቀርብለት፣የሚተቸው፣የሚቃወመው ስለሌለ ያሻውን ጥፋት ለመፈፀም አስችሎታል፣ እውን ለኢትዮጵያ በጎ ነገር አስቦ? ስንት አንገብጋቢና በአቅም ሊስሩ የሚችሉ በርካታ ችግሮች ማከናወን ሲቻል የአገር ሃብት የሚያባክን ስራ መጀመሩ አገሪቱንና ህዝቡን ደጋግሞ የመግደል ተግባር ነው፣ አሁን ወቅቱስ ነበር ወይ? ሌላ አማራጪስ የለምን? እንደ ዋቢ ሸበሌ፣ያን ያህል ርቀትስ ድንበር ላይ ለምን ተመረጠ? ነፍጠኛው መለስ ዜናዊ ከሱዳን ጋር ካደረገው ምስጢራዊ ስምምነት ሌላ አንዱንም የግልገል ግቤ በቅጡ ላልገነባው “ሳሊኒ” ለተባለው የጣልያን ኩባንያ ያለ ጨረታ መስጠቱ ሌላው ምስጢራዊ ተግባር ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ጥንት ያገኝ የነበረውን የመብራት አገልግሎት ተነፍጎ፣ ኤምባሲዎች በሙሉ ጄኔሬተር እንደሚጠቀሙ እየታወቀ ለጅቡቲና ሱዳን መብራት መሽጥ ጀምረናል እያለ መለስ ዜናዊ ዘወትር በኢቲቪ በድፍረት ያለመታከት ማውራቱ አገሪቷን ምን ዓይነት ማፈርያ ስው እየመራት እንደሆነና ለሚገዛው ህዝብ ደንታ ቢስ መሆኑን አሳይቶ አልፏል፣ ሱዳንና ግብፅ በአባይ ጉዳይ ቀልድ እንደማያቁ የህልውናቸውም መስረት መሆኑ፣ ዓባይን መንካት ማለት በሁለቱ አገራት ህዝቦች ላይ የሞት ፍርድ ከመስጠት ይቆጠራል እያሉ ለዘመናት ተናግረዋል አሁን ታድያ በሚዲያዎች በሙሉ “ዓባይ ይገደባል” እየተባለ በየዕለቱ ሲፎከር፣ጉራ ከረዩ ሲባል እውን ሊገደብ ነው? ከተማዋ ግን መሟሟቅ ጀምራለች ስራተኛና ወዝአደሩ የምግብና የባር ሌላም አገልግሎቶችን ያገኛል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ ከስሞኑ የሳውዲ ልዑልና የመከላከያ ም/ሚኒስትር ካሊድ ቢን ሱልጣን በግብፅ ምድር በተደረገው የውሃ ሃብት ልማት ስብስባ ላይ ተገኝቶ ግድቡ “የተስራበት ቦታ ከስባት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ በመሆኑ ቢፈርስ የታች አገሮችን ያጠፋቸዋል ስለዚህ ዓላማው የተንኮልና ሆን ተብሎ አረቦችን ለማጥቃት የታቀደ ነው” በማለት ዛቻ ዓይነት መግለጫ ስጥቷል፣ የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንዲሉ ግብፅና ሱዳን ሙያ በልብ ነው ብለው ብዙ ባላሉበት ጉዳይ የሳውዲ ጦር ሚኒስትር ዲፕሎማሲን ባልተከተለ ሁኔታ ያውም ሳውዲ ስታር ግሩፕ በቅርብ ርቀት በሚያርስበት አካባቢ ይህን ዓይነት ዛቻ አዘል መግለጫ መስጠቱ መልዕክቱ ትኩረት የሚያሻው ነው፣ እንደማስጠንቀቂያም ሊወስድ ይችላል። ይህ የሚያሳየው ግብፅም ሱዳንም በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ነው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ግብፆችና ሱዳኖች በመላ አገሪቱ ከነዋሪው የበለጠ መንደሮችን ሁሉ ሳይቀር ያለከልካይ እንደልብ የሚዘዋወሩት ለሽርሽር ሳይሆን በዓባይ ጉዳይ መሆኑን ማወቅ ያሻል፣ በፈለጉበት ስዓት ያሻቸውን ማድረግ እንደሚችሉ ማወቅ ያስፈልጋል፣ ጠንካራ የሆነ የሁሉንም ድጋፍ በቀላሉ ያገኛል፣ በመሆኑም መንግስታት በሙሉ ከጠንካራው ጋር ይቆማሉ፣ቱርክ ዩፍሬትስና ቲግሪስ ወንዞችን ስትገድብ ጠንካራዋ የሳዳም ሁሴን ኢራክና ሶርያ አንገት ደፍተው ትንፍሽ ሳይሉ የመዓቱን ግዜ አሳልፈዋል፣ ጉልበት ማማሩ፣ ወዳጅ አልባዋ የመለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ግብፅ መዓቱን ብታወርድባት የማን ያለህ ይባላል፣ ሁሉም የማርያም ጠላት ነው የሚያደርገን ፣የተባበሩት መንግስታት ቀርቶ የአፍሪካ ህብረት የሚተቸው አይሆንም።
የግብፅ የመከላከያ ኃይል ምን ይመስላል
ም/ጦር--- AI MI ABRAMS TANK በአሜሪካ ላይስንስ ግብጽ ውስጥ ይስራል፣ በጦር ኃይል ከአፍሪካ አንደኛ---የቅኝት ሳተላይት ካላቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ናት---ተጨማሪ ሳተላይት በ2007 ልካለች----በኔቶ የመዲተራንይን ውይይት መድረክ ተካፋይ--የግብፅ 40% ኤኮኖሚ የጦር ኃይሉ ነው አየር ኃይል---ከአፍሪካ አንደኛ--230-ኤፍ16-ይህን ተዋጊ ጄት በመጠቀም ከአለም 4ኛ--530 ተዋጊ ጄት ሲኖራ--ሚራዥ--ሚግ 29--ያካትታል---150ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች የአየር መከላከያ ዕዝ--አየር መቃወሚያዎች---ሮኬትና ሚሳይል ክንፍ---ኢንተርሴፕተር ተዋጊ ጄቶች---ራዳርና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ክንፍ-- የባህር ኃይል-- የአረብ ኢንዱስትሪ ድርጅት(ግብፅ፣ሳውዲና አረብ ኢሜሬትስ)ያቁዋቁዋሙት ሲሆን ሁለቱ 2ቢሊዮን ኢንቨስት አድርገው ጥለው ወጥተዋል--ከ12 በላይ ኢንዱስትሪዎችና 19ሺ ስራተኞች አሉት-- የአረብ ቴክኖሎጂ ተቁዋም-- ወታደራዊ ት/ቤቶች-- ዕዝና ስታፍ ኮሌጅ-- ተጠባባቂ መኮንኖች ኮሌጅ-- የናስር ሚሊተሪ አካዳሚ-- የግብፅ ሚሊታሪ አካዳሚ-- የግብፅ አየር አካዳሚ-- የግብፅ አየር መከላከያ አካዳሚ-- የግብፅ ወታደራዊ ተ/ዕድ ኮሌጅ
ግብፆች ሱዳን ጠረፍ ካለው ኤር ቤዝ በመነሳት ማንኛውንም የኢትዮጵያ ምድር በቀላሉ ማጥቃት ይችላሉ፣ ከአፍሪካ አንደኛ የሆነውን ኃይል ለመከላከል ኢትዮጵያ ምን አይነት ስራኣዊት አላት
--ከ 170 የማይበልጡ ያረጁ ሶቬየት ስራሽ ቲ-55 እና 50 ቲ-62 እንዲሁም ከየመን የተገዙ 50 ቲ 72 ታንኮች ---150000 –180000 በቅጡ በወታደራዊ ሙያና ዲሲፕሊን ያልተገነባ ስራዊት--
በዚያ ላይ የወያኔ መከላከያ እንደሚታየው እርስ በርሱም ያልተግባባና ችግር ውስጥ ያለ ስለመሆኑ በቅርቡ በቡሬ ግንባር የታየው የርስ በርስ ዕልቂት ብቻ በቂ ማስረጃ ነው፣በዚህ አይነት ውስጡ ቢገባ ስንት ጉድ አለ፣ እንዲሁ በወፍ በረር መቃኘትም ይቻላል፣ ስራዊቱ በውትድርና ሙያው በዲስፕሊን የላቀና ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃይል፣የተሟላ ትጥቅ የለውም፣ አየር ኃይል ከኤርትራ መሻሉ ካልሆነ በቀር አለ ማለት አይቻልም፣ ኤር ድፌንስ ሲስተም የተረሳ ነው፣ ግብፅ በፈለገቺው ስዓት የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሳ የፈለገችውን ስፍራ ማጥቃት ብታደርግ የሚያቆማት የለም፣ ዩኒፎርም ማልበስና የመሳርያ ፋብሪካ ማቁዋቁዋም ብቻ ጥንካሬን አያመለክትም፣ከግብፅ ጋር ውጊያ መግጠም አይሞከርም፣ ከነሱ ጋር ማነፃጸርም ድፍረት ነው፣ከደርግ ግዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ በእጅጉ ወድቁዋል፣ ግብፆች እንደ ድርቡሽ ዘመን እግረኛ ጦር መላክ አያስፈልጋቸውም፣ የፈለጉትን ዒላማ እዚያው ሆነው መምታትም ይችላሉና።
በመሆኑም የመለስ ዜናዊ ፍላጎት በዓባይ ግድብ ስም ያለማቁዋረጥ መዋጮ መስብስብ ነው፣ መዋጮ ማዋጣት ህዝቡ ሲያቆም ትያትሩም ጨዋታውም እዚያ ላይ ይዘጋል/ ይቆማል፣ ሌላው ኢትዮጵያን ያለወቅቱ ከግብፅ ጋር በማጋጨት ወደፊት በዚህ ዙርያ እንዳታቅድ ማድረግ ነው የሚል እምነት አለኝ ሆኖም ግን ኢህአዴግ ሌላ በስልጣን የመቆያ ዘዴ እስኪፈጥር ወይም ጠንካራ ተተኪ እስኪያገኝ ድርስ መቃብር የወረደውን አሁንም ወደፊትም የክቡር አቶ መለስ ራዕይ ተግባራዊ እናደርጋልን መፈክር ይቀጥላል፣ ህዝቡ ግን ተዋሽም አልተዋሽም ማድመጥ አቁሟል፣ ኢህአዴግም መለስ ዜናዊ ዓይነት ዋሾ ከየትም እንደማያመጣ ታውቁዋል ከዚህ በሁዋላ በቡሬ ግንባር የተጀመረው የኢህአዴግ የርስ በርስ ሽኩቻና መጠፋፋት ትያትር መመልከት የኢትዮጵያ ህዝብ ተራ ይሆናል። የአባይ ግድብ ግን በአቅም ያልተጀመረ በመሆኑ ህልም ሆኖ ይቀራል ማለት ይቻላል።
አስጨናቂ ድረስ (ከጉለሌ) baschenaki44@gmail.com

No comments:
Post a Comment